ቀን 25 /11/2014 ዓ.ም

የተማሪዎች ማርች ባንድ ትንሳኤ

ተማሪዎች ከትምህርታቸዉ ጎን ለጎን ክህሎታቸዉን የሚያዳብሩበት እንዱ ማዕከል እንደሆነ የሚጠቀስለት የተደራጀ የተማሪዎች የሙዚቃ ባንድና ማርች ባንድ ከ43 ዓመታት በፊት ከነበረባቸዉ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ የሆነዉ ዳግማዊ ሚኒሊክ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነዉ፡፡ በትምህርት ቤቱ ከ43 አመታት በፊት ተቋርጦ የነበረዉ የተማሪዎች ማርች ባንድ ዘንድሮ ትንሳዩዉን እድርጋል፡፡

በ50 ተማሪዎችን በማስልጠን ስራዉ መጀመሩን የሚናገሩት የሙዚቃ ሙያተኛ እና መምህር የሆኑት ሌተናል ኮሎኔል ሲሳይ ፍቃዱ ለትንሳዩዉ ምክንያት ሆነዋል፡፡ ሙያተኛዉ የግል የሙዚቃ መሳሪያቸዉን ተማሪዎች በነጻ እንዲጠቀሙባቸዉ በማድረግ እና ስልጠና በመስጠት የተማሪዎች ማርች ባንድ እንዲጠናከር ሰፊ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

የሙዚቃ መሳሪዎችን ጡረታ ከወጡ በሃላ እንደገዛቸዉ የገለጹት ሌተናል ኮሎኔል ሲሳይ ፍቃዱ ተማሪዎችን በፍላጎታቸዉ መስረት በመልመል በነጻ ስልጠና በመስጥ ላይ መሆናቸዉን ያሳወቁ ሲሆን ተማሪዎችም ባገኙት ስልጠና መሰረት በተማሪዎች ማርች ባንድ መቋቋም ላይ የድርሻቸዉን እየተወጡ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ አክለዉም በሌሎች ትምህርት ቤቶች ላይም እንዲስፋፋ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ብለዋል፡፡

የማርች ባንድ አባል የሆኑ እና የዝግጅት ክፍላችን ያነጋገራቸዉ ተማሪዎችም በስልጠናዉ ደስተኛ መሆናቸዉን በመግለጽ ለሌተናል ኮሎኔል ሲሳይ ፍቃዱ እና ለትምህርት ቤቱ ምስጋና አቀርበዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከ43 ዓመታት በፊት የሙዚቃ ትምህርትን በማጠናከር ተማሪዎች በፍላጎታቸዉ በትምርት ቤት ውስጥ የተቋቋሙ የተማሪ ባንዶችና እና ማርች ባንዶችን እንዲቀላቀሉ በማድረግ በዘርፉ ለሀገር ፈርጥ የሆኑ ታዋቂ ሙዚቀኞችን ለማፍራት መቻሉን ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

One thought on “ቀን 25 /11/2014 ዓ.ም

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s