የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የለውጥና መልካም አስተዳደር ቡድን ከሀምሌ 18/2014 ዓ.ም ጀምሮ ሲያካሂድ የቆየውን የ2014 በጀት ዓመት የትምህርት ተቋማት የቢ ኤስ ሲ ስኮር ካርድ እቅድ አፈጻጸም ምዘና ማጠናቀቁን አስታወቀ።
ምዘናው በሁሉም የመንግስት አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣በክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች እንዲሁም በማዕከል ደረጃ ተካሂዶ በዛሬው እለት መጠናቀቁን የቢሮው የለውጥና መልካም አስተዳደር ቡድን መሪ ወይዘሮ እጸገነት አብዱ ገልጸው በሂደቱም 324 መዛኞችና 22 አስተባባሪዎች መሳተፋቸውን አስታውቀዋል።
ቡድን መሪዋ አክለውም ምዘናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ከመመዘኛ መስፈርት ዝግጅት ጀምሮ ለመዛኞችና አስተባባሪዎች ኦረንቴሽን ተሰጥቶ ወደ ምዘና መገባቱን ጠቁመው የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ተቋማት የምዘና ውጤቱን መሰረት በማድረግ እውቅና እንደሚሰጣቸው አስገንዝበዋል።
ምዘናው ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ መዛኞችና አስተባባሪዎችን ጨምሮ ለተመዛኝ ተቋማት ላቅ ያለ ምስጋና እንደሚገባቸው ቡድን መሪዋ አስረድተዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
