ቀን 21/11/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ስራተኞች ለአትሌቶች የምስጋና መርኃ ግብር አካሄዱ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ዲዛይንና ግንባታ ቢሮዎች ስራተኞች ጀግኖች አትሌቶች በ18ኛው አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላስመዘገቡት ድል የምስጋና መርኃ ግብር አካሄዱ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፎ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ አትሌቶቻችን ባስመዘገቡት አንፀባራቂ ድል ዙሪያ ያስተላለፉት መልዕክት ባለፉት ጥቂት ዓመታት እንደ ሀገር ፈተና ያጋጠመን ቢሆንም ለችግሮቻችን ስንበረከክ የኢትዮጵያን አኩሪ የድል ታሪክ መጻፍ የቻልን ትውልድ በመሆናችን ደስታ ይሰማናል ፤ በአንድነት የማሽነፍ እሴትንም አጠናክረን ልናስቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡ አክለውም ምስጋናን ባህል በማድረግ የተሻለ የሰራን በማመስገን ለላቀ አፈጻጸም መትጋት ውጤታማ የሚያደርግ በመሆኑ በመመሰጋገን እና በጽናት በመጓዝ የበለጸገች ሀገርን ለመፍጠር በትኩረት መስራት ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ክብርት ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም ይህ ታሪክ የኢትዮጵያን ጥንካሬ ፤ የኢትዮጵያን ሀያልነት ፤ የኢትዮጵያን አልበገር ባይነት ለማየት ለማይፈልጉት ሐገራት ጥሩ ማሣያ ሲሆን በተያያዥነትም ይህ ታሪካዊ ኩነት ደግሞ በሀገረ አሜሪካ  ምድር ላይ በደማቅ ቀለም  መፃፉ ከታሪክም፤ ከድልም በላይ ልዩና ጣፋጭ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በብዙ ፈተናና ውጣ ውረድ ብትፈተንም በፅናት ተቋቁማ ያገኘችውን ድል በማስመልከት ነው ለጀግኖች አትሌቶች የምስጋና መርኃ ግብሩ የተካሄደው፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s