ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ከዓለም ደግሞ 2ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ በሻምፒዮናው ታሪክ ከፍተኛው ሜዳሊያ በማግኘት አጠናቃለች፡፡
ላለፉት 10 ቀናት በአሜሪካ ኦሪገን ሲካሄድ የሰነበተውን 18ኛውን የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛውን ሜዳሊያ በማግኘት አጠናቃለች፡፡
በወንዶች እና ሴቶች ማራቶን እንዲሁም በ10ሺ እኛ 5 ሺ ሜትር ሴቶች 4 ወርቅ በማምጣት በሻምፒዮናው ከፍተኛ የሚባል ውጤት ተመዝግቧል፡፡
በ3ሺ ሜትር መሰናክል በሴት እና ወንድ እንዲሁም በወንዶች ማራቶን እና በ1500 ሜትር ሴቶች የብር ሜዳሊያ ተገኝቷል፡፡
ሁለቱ የነሐስ ሜዳያ የመጣው ደግሞ በሴቶች 3ሺ መሰናክል እና በ5ሺ ሜትር ነው፡፡
ኢትዮጵያ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከአፍሪካ ቀዳሚ ፣ ከዓለም ደግሞ ከአሜሪካ በመቀጠል 2ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ በሻምፒዮናው ታሪክ ከፍተኛው ሜዳሊያ በማግኘት አጠናቃለች፡፡
ጎረቤት ኬንያ ደግሞ በ2 ወርቅ ፣5 የብር እና 3 የነሀስ በድምሩ 10 ሜዳሊያ በማግኘት በኢትዮጵያ በሁለት ወርቅ ተበልጣ ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!









