የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዲሱ ስርዓተ ትምህርትን መሰረት በማድረግ የሬዲዮ ትምህርት ይዘት መረጣ ማከናወን ጀመረ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ትምህርት ቢሮ ኤፍ ኤም 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተተረጎመውን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ ለአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች እገዛ የሚያደርግ የሬዲዮ ትምህርት ዝግጅት የይዘት መረጣ በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች ማድረግ መጀመሩን አሳወቀ፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተዘጋጅቶ ወደ ሙከራ ትግበራ ከገባ በሀላ በአሁኑ ሰሃት የመጻህፍት ህትመት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዉ ቢሮዉ ዝግጅቱን በከተማዉ መምህራን ፣ ባለሙያዎች እና የትምህርት አመራሮች አቅም እንዲከናወን ማድረጉ የሚመሰገን ተግባር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ አበበች አክለውም በቀጣይ በ2015 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባ በመሆኑ ለሬዲዮ ትምህርት ዝግጅት ያግዝ ዘንድ የይዘት መረጣዉ ላይ ለመሳተፍ የተገኙ አካላት ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ አደራ ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ቴክኖሎጂ ልማት እና ትግበራ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በለጠ ንጉሴ የትምህርት በሬዲዮ ዝግጅቱን አስመልክተዉ በሰጡት ማብራሪያ በመጀመሪያ ዙር የተዘጋጀዉ የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የሬዲዮ ትምህርት ይዘት መረጣ ሲጠናቀቅ ይዘት መረጣው ምክረ ሀሳብ እንዲሰጥበት ከተደረገ በሃላ ወደ ሙሉ የሬዲዮ ስክሪፕት ጽሁፍ ዝግጅት ሂደት የሚሻገር እና በቀጣይም ወደ ድምጽ ቀረጻ ዝግጅት የሚገባ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ትምህርት ቢሮ ኤፍ ኤም 94.7 የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያ ቡድን መሪ ወ/ሮ በላይነሽ የሻው በበኩላቸዉ በዝግጅቱ ላይ የሚሳተፉት ከአስራአንዱም ክፍለ ከተማ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት በማዘጋጀት ላይ የተሳተፉ መምህራን፣ የስርዓተ ትምህርት ትግበራ ባለሙያዎች እንዲሁም የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጆች ናቸዉ ብለዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!









