የትምህርት ተቋማትን ለመማር ማስተማር ስራው ምቹ ለማድረግ የሚያስችል የመስክ ምልከታ ተካሄደ፡፡
ምልከታው የተካሄደው በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 5 እና 12 በሚገኙት ቡቃያ አንደኛ ደረጃ እና በካራ ገቢሳ ሳተላይት ትምህርት ቤቶች ላይ ሲሆን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መራጊያ ተበጀ ትምህርት ቤቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
የጉብኝቱ ዓላማ በመጪዉ 2015 ትምህርት ዘመን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ያለባቸዉን ትምህርት ቤቶች ችግር ለመፍታት እና ሳተላይት ትምህርት ቤቶች ትኩረት አግኝተው ደረጃዉን የጠበቁና ጥራት ያለው ትምህርት ለተማሪዎች እንዲሰጡ በሚያስችል መልክ አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶችን ለማድረግ እንደሆነ አቶ መራጊያ በምልከታው ወቅት መናገራቸውን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!



