ቀን 14/11/2014 ዓ.ም

የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት አመራሮች ፣ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ከደሞዛቸው በማዋጣት ለ133 የተማሪ ወላጆች ማዕድ አጋሩ።

በማዕድ ማጋራቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰግደው ሀ/ጊዮርጊስ ባስተላለፋት መልዕክት አለማቀፋዊ የሆነው የኑሮ ውድነት ማለፍ የምንችለው በኢትዮጲያዊ እሴታችን መደጋገፍ፣ መረዳዳትና ያለውን ተካፍሎ መብላት ስንችል ነው ብለው ይህንን በጎ ተግባርም በክ/ከተማው በሁሉም ቦታ እየተገበርን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጲያዊነት በመስጠት፣ በመደጋገፍ፣ በመረዳዳት፣ በአብሮነትና አንዱ የአንዱን ችግር በመካፈል ላይ የተመሰረተ ነው ያሉት አቶ አሰግደው ወቅቱ መረዳዳትና መተጋገዝን የሚጠይቅ በመሆኑ ከመቸውም ጊዜ በላይ መረዳዳትን ማጎልበት ይኖርብናልም ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ በበኩላቸው ሰው ተርፎት ሳይሆን ከጉድለቱም ይሰጣል፤ ይህንን ደግሞ የክ/ከተማው የትምህርት አመራሮች፣ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በተግባር አረጋግጠዋል ብለው በአብሮነትና በመተጋገዝ ችግሮቻችንን ሁሉ መሻገር ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል።

የክ/ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት እጅግአየሁ አድማሱ በበኩላቸው በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር በጎነት ለዘላቂ  አብሮነት የሚል መርህ አንግበን  ትምህርት ተቋማትን በማስተባበር  የአረንጓዴ አሻራ ፣ ማዕድ ማጋራት፣ የማጠናከሪያ ትምህርትና የተለያዩ ድጋፍችን እያከናወን ነው ብለው በዛሬው እለትም ለ133 የተማሪ ወላጆች ማዕድ በማጋራት የበጎ ተግባር ስራችንን አጠናክረን ቀጥለናል ብለዋል።

ድጋፉ የተደረገው የትምህርት አመራሩ ፣መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ከደሞዛቸው በማዋጣት ነው ያሉት ኃላፊዋ የበጎ ፈቃድ ስራው በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በእለቱም የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርቱና የጓሮ አትክልት ልማት ጉብኝት ተደርጓል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

 ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s