ቀን 13/11/2014 ዓ.ም

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲሰጥ የነበረዉን የምገባ ፕሮግራም ሂደትን ኦዲት ማድረጉን ገለፀ፡፡

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በ2014 የትምህርት ዘመን በአስራ አምስት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተከናወነዉን የምገባ ፕሮግራም በተመለከተ አጠቃላይ ሂደቱ ምን እንደሚመስል ውይይት አድርጋል።

በሪፖርቱ ከሀምሌ 1/2013 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30/2014 ዓ.ም በምገባ ፕሮግራሙ የተሠሩ ስራዎችን መሠረት ተደርጎ የተሠራ ስለመሆኑ ሲገለፅ የዚህ የኦዲት ስራም ዋናው አላማም የትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮግራም መንግስት ለምገባ ፕሮግራሙ የሚያወጣውን ወጪ ለታለመለት አላማ መዋሉን ለማረጋገጥ እና በምገባ ፕሮግራሙ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን የመፍትሔ ሀሳብ ለማስቀመጥ ያለመ እንደሆነ ተጠቁሟል።

መድረኩን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ድርጅት ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተሾመ ክፍሌ፣ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ባዩማ ወረቁ እና የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገመቺስ ዋቅጅራ መርተውታል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ድርጅት ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተሾመ በመድረኩ እንደ ክፍተት የታዩ ችግሮችን ወስዶ ማስተካከል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የለሚኩራ ክፍለ ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ባዩማ በበኩላቸው በኦዲቱ የተገኙ ክፍተቶች ካለፈው ትምህርት ወስደን ለወደፊቱ ማስተካከል ያለብንን ማስተካከል ይገባል ብለዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

 ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s