ቀን 13/11/2014 ዓ.ም

የክረምት ትምህርትን ለማበረታታት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉ ተገለፀ፡፡

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እና ትምህርት ጽ/ቤት አስተባባሪነት የክረምት በጎ ፍቃድ የክረምት ትምህርት ማጠናከሪያ እየወሰዱ ላሉ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉ ተገለፀ።

ይህ ድጋፍ በክረምቱ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እየተከታተሉ ያሉ ተማሪዎችን ለማበረታታት ያለመ ስለመሆኑ በድጋፉ ወቅት የተነሳ ሲሆን በዚህ የበጎ ፍቃድ ስራ ላይም የመንግስት ሠራተኞች ያላቸውን ትርፍ ሰአት ሰውተው ከበጎ ፍቃደኛ መምህራን ጋር እየሠሩ ስለመሆናቸውም ተጠቁሟል።

በዚህ የድጋፍ ስነ-ስርአት ላይ የተገኙት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ባዩማ በንግግራቸው የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለሀገሩ እና ለወገኑ ጠቃሚ ዜጋ ለማድረግ ትምህርት የሁሉም ነገር ቁልፍ መሆኑን ገልጸው እንደዚህ አይነት ድጋፎች ላይ ለትውልድ አሳቢ የሆኑ ባለሀብቶች ፣ ግለሠቦች እና ተቋማት ተሳትፎ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎ እና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ኬኔ የትምህርት ቁሳቁሱን ለተማሪዎች ባስረከቡበት ወቅት እንደገለፁት በክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች አንዱ በሆነው የክረምት በጎ ፍቃድ ትምህርት አሠጣጥ ሂደት ላይ የትምህር ቁሳቁስ እጥረት እንቅፋት እንዳይሆን ድጋፉ መደረጉን ተናግረዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

 ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s