በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከ400 በላይ ለሆኑ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ፡፡
የቻይናው በጎ አድራጎት ድርጅት ሲ ሴፍ ፒ ኤ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፊሊጶስ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ከ400 በላይ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉ ከቻይናው በጎ አድራጎት ድርጅት ሲ ሴፍ ፒ ኤ የተገኘ ሲሆን የቦርሳና ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው፡፡
ድጋፉንም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ እና የቻይናው የኢኮኖሚ ጉዳዮች ኮንሱላር ያንግ ዪ ሃንግ ማስረከባቸውን የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ተማሪዎችን ማገዝ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ መቅረፅ ነው ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እንደገለጹት የትውልድ ግንባታ ስራ የሆነውን ትምህርትን መደገፍ የሁሉም ኃላፊነት በመሆኑ በጋራ ተባብረን የነገ ሀገር ተረካቢ ልጆችን ማገዝ ይገባል ብለዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!



