ቀን 1/11/2014 ዓ.ም

ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1ሺህ 443ኛው ዓመት ሒጅራ የኢድ አል አድሃ በዓል አደረሳችሁ፡፡

በሀገራችን ከምናከብራቸዉ ታላለቅ ሀይማኖታዊ በዓላት አንዱ ታላቁ የኢድ አል አድሃ በዓል በመሆኑ እንኳን ለበአሉ በሰላም አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡

በዓሉን ስናከብር እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የተቸገሩትን በመርዳት ፣ በመደጋገፍና በመተሳስብ ከሁሉም በላይ አብሮነታችንን በማጠናከር ሊሆን ይገባል፡፡

በዓሉ የህዝባችን የአንድነትና የአብሮነት መገለጫ እሴት ከመሆኑም ባሻገር የኢትዮጵያዊነት ማሳያ እና መገለጫ በመሆኑ በዓሉን ስናከብር የብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ የሆነችዉ ሀገራችን የውበት ማሳያ የእንድነታችን ቀንዲል መሆናን አጉልተን  የምናሳይበት ታላቅ እለት መሆኑን በማሰብ ሊሆን ይገባል፡፡

ከዚህም ባለፍ ሀይማኖታዊ ወንድማማችነት እና እህታማችነታችንን የምናጠናክርበት አንተ አንቺ ትብሽ የምንባባልበት ታላቅ እና የሀገራችንን እና የህዝባችንን ከፍታ ወደ ላቀ ደረጃ የምናሻግርበት እለት እንዲሆን እመኛለሁ፡፡

በድጋሜ እንኳን ለ1ሺህ 443ኛው የኢድ አል አድሃ በዓል በሰላም ፣ በፍቅር ፣ በጤናና በአንድነት አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡

                                    ዒድ ሙባረክ !

                                   ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

                                     አቶ ዘላለም ሙላቱ

                         የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

 ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s