ቀን 29/10/2014 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሰኔ 27 ጀምሮ በ179 የፈተና ጣቢያዎች ሲሰጥ የቆየው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና  በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ያለምንም እንከን መጠናቀቁን የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በዘንድሮው የ8 ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 6,769 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበው 6,729 የሚሆኑት  በ12 የፈተና ጣቢያዎች መፈተናቸውንና ይህም አፈጻጸሙ 99.4% መሆኑን የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለልኝ ወልዴ ገልጸዋል።

ኃላፊው አክለውም በፈተና ሂደቱ 206 ፈታኞችን ጨምሮ 70 ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም 26 ጣቢያ ኃላፊዎችና ከ240 በላይ የፖሊስ አባላት ተመድበው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣታቸውን ገልጸው ፈተናው በክፍለከተማው በሁሉም ጣቢያዎች ያለምንም እንከን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲካሄድ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የኮማንድ ፖስት እንዲሁም የጸጥታ አካላትን ጨምሮ በየደረጃው ለሚገኙ የፈተና አስፈጻሚዎች ምስጋና  አቅርበዋል።

ቀርሳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በክፍለ ከተማው ፈተናው ከሚሰጥባቸው የፈተና ጣቢያዎች መካከል አንዱና በክፍለ ከተማው ሙሉ ለሙሉ በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ትምህርት የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ሲሆን በጣቢያው 94 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን የፈተና ጣቢያው ኃላፊ አቶ ሞቱማ በልአ ገልጸው ፈተናውም ያለምንም ችግር መጠናቀቁን አስታውቀዋል ።

ፈተናው በዛሬው እለት ሲጠናቀቅ በቀርሳ አጸደ ህጻናትና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተፈታኝ ተማሪዎች እንዲሁም በክፍለ ከተማው እና በወረዳ 11 አመራሮች “አረንጓዴ አሻራችን ለትውልዳችን” በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተካሂዷል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

 ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s