“ሞት ካልቀደመኝ እስከ ዩኒቨርስቲ ቀጥዬ መማር እፈልጋለሁ” የሚሉት የ53 ዓመቱ የ8ኛ ክፍል ተፈታኝ አባ ዘውገ በቀለ፡፡
አባ ዘውገ ፈተናውን እየወሰዱ የሚገኘው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር በቃሊቲ ቅድመ መደበኛና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው፡፡
አባ ዘውገ ትምህርታቸውን በማታዉ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ሲከታተሉ ቆይተዋል፡፡
እኚህ አባት ሁሉም ሰው በዕድሜና በመሰል ጉዳዮች ሳይረታ ባገኘው አጋጣሚ መማር አለበት፤ እኔም ሞት ካልቀደመኝ እና ፈጣሪ ከረዳኝ እስከ ዩኒቨርሲቲ በመቀጠል በማገኘዉ ዕዉቀት ህዝቤን አገለግላለሁ ፈጣሪ ሀገራችንን እና ህዝቦቿን ይባርክ ብለዋል።
የወረዳው ትምህርት ጽኅፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢፋ አብሼ በበኩላቸው፥ “ትምህርት ዕድሜን አይገድብም ፤ ሁሉም ሰው ለመማር አዕምሮውን ዝግጁ ካደረገ የሚገድበው ነገር እንደሌለ እኚህ አባት ለዘመኑ ትዉልድ ትልቅ ማስተማሪያ ናቸው” ብለዋል፡፡
ትምህርት ተቀጥሮ ለመስራት ብቻ ሳይሆን ለኅሊና እርካታ ጭምር መሆኑንም የአባ ዘውገ ታሪክ ትልቅ ማስተማሪያ መሆኑን ነው ኃላፊው ያነሱት፡፡
የወረዳው ትምህርት ጽኅፈት ቤት ኃላፊው ለአባ ዘውገ መልካም የፈተና ጊዜ እና ጥሩ ውጤትም ተመኝተዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!


