በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ179 የፈተና ጣቢያዎች ትላንት መሰጠት የጀመረው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በዛሬው እለት በልደታ ክፍለ ከተማ ሰላማዊ በሆነ መልኩ መካሄዱን የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በዘንድሮው የ8 ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በልደታ ክፍለ ከተማ 3,573 ተማሪዎች በ12 የፈተና ጣቢያዎች ፈተናውን በመውሰድ ላይ እንደሚገኙና 103 ፈታኞችን ጨምሮ 34 ሱፐርቫይዘሮችና 12 ጣቢያ ኃላፊዎች ተመድበው በስራ ላይ እንደሚገኙ የክፍለከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ እጅጋየሁ አድማሱ ገልጸው በክፍለ ከተማው ፈተናው ከትላንትናው እለት ጀምሮ ሰላማዊ በሆነና በተረጋጋ መንፈስ በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
አለማያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በክፍለ ከተማው ፈተናው ከሚሰጥባቸው የፈተና ጣቢያዎች መካከል አንዱ ሲሆን በጣቢያው 268 ተማሪዎች ፈተናውን በመውሰድ ላይ እንደሚገኙና 8 ፈታኞችና 3 ሱፐርቫይዘሮችን ጨምሮ የፖሊስ አባላት ተመድበው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት ላይ እንደሚገኙ ከፈተና ጣቢያው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!


