በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ179 የፈተና ጣቢያዎች ትላንት መሰጠት የጀመረው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በዛሬው እለትም በአራዳ ክፍለ ከተማ ሰላማዊ በሆነ መልኩ መካሄዱ ተገለጸ።
በዘንድሮው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በአራዳ ክፍለ ከተማ 3,678 ተማሪዎች በ10 የፈተና ጣቢያዎች ፈተናውን በመውሰድ ላይ እንደሚገኙና 95 ፈታኞችን ጨምሮ 35 ሱፐርቫይዘሮችና 10 ጣቢያ ኃላፊዎች ተመድበው በስራ ላይ እንደሚገኙ የክፍለከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ገልጸው በክፍለ ከተማው ፈተናው ከትላንትናው እለት ጀምሮ ያለምንም የጸጥታም ሆነ ሌላ ችግር በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
ዳግማዊ ሚኒሊክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በክፍለ ከተማው ፈተናው ከሚሰጥባቸው የፈተና ጣቢያዎች መካከል አንዱ ሲሆን በጣቢያው 437 ተማሪዎች ፈተናውን በመውሰድ ላይ እንደሚገኙና 12 ፈታኞችና 5 ሱፐርቫይዘሮችን ጨምሮ የፖሊስ አባላት ተመድበው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት ላይ እንደሚገኙ የፈተና ጣቢያው ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ሙሉነህ ገልጸዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!




