በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ በ179 የፈተና ጣቢያዎች በመሰጠት ላይ የሚገኘው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በጉለሌ ክፍለ ከተማ ያለምንም እንከን መካሄዱ ተገለጸ።
በክፍለ ከተማው ፈተናው ከሚሰጥባቸው የፈተና ጣቢያዎች መካከል አንዱ በሆነው ጄነራል ታደሰ ብሩ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን ሲከታተሉ ያገኘናቸው የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራ በሰጡን አስተያየት በክፍለ ከተማው በ20 የመፈተኛ ጣቢያዎች 5,530 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን ገልጸው ፈተናው በሁሉም ጣቢያዎች ያለምንም እንከን ሰላማዊ ሆኖ መካሄድን አስታውቀዋል።
የጄነራል ታደሰ ብሩ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ዳባ ተረፈ በበኩላቸው በትምህርት ቤቱ 318 ተማሪዎች ፈተናውን በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው ፈተናው በጣቢያው በተያዘለት ሰአት ተጀምሮ ያለምንም ችግር መጠናቀቁን አስረድተዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!



