በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ በ179 የፈተና ጣቢያዎች በመሰጠት ላይ የሚገኘው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በቦሌ ክፍለ ከተማ ያለምንም እንከን መጀመሩ ተገለጸ።
በክፍለ ከተማው ፈተናው ከሚሰጥባቸው የፈተና ጣቢያዎች መካከል አንዱ በሆነው አዲስ ራዕይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን ሲከታተሉ ያገኘናቸው የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ታጋይቱ አባቡ በሰጡት አስተያየት በክፍለ ከተማው በ14 የመፈተኛ ጣቢያዎች 5,081 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን ገልጸው ፈተናው በሁሉም ጣቢያዎች ያለምንም እንከን ሰላማዊ ሆኖ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በክፍለ ከተማው የወረዳ 5 ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ግዮን በበኩላቸው በአዲስ ራዕይ ትምህርት ቤት የትምህርት ቤቱን ጨምሮ የግሎሪ እና ጊብሰን አካዳሚ ተማሪዎች ፈተናውን በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው ፈተናው በጣቢያው በተያዘለት ሰአት መጀመሩን አስረድተዋል።
በፈተና ጣቢያው በዛሬው እለት 351 ተማሪዎች በፈተና ጣቢያው መገኘታቸው የተገለጸ ሲሆን የጥዋት ፈረቃ ፈተና ተፈትነው ሲውጡ አስተያየታቸውን የሰጡን ተማሪዎች ፈተናቸውን ያለምንም የጸጥታም ሆነ ሌሎች ችግሮች ተፈትነው መውጣታቸውን ገልጸዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!






