ቀን 25/10/2014 ዓ.ም

የቤት እድሳት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት አስተባባሪነት በወረዳ 03 አስተዳደር የቤት እድሳት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ።

የቤት እድሳቱን ሙሉ ወጪ የሚሽፍኑት ዳይመንድ እና በቀድሞ ስሙ በሻሌ በአሁን ስያሜው ደግሞ ማርይዞና ት/ቤቶች ሲሆኑ የቤቱ ሙሉ እቃ ወጪ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሚሽፈን ይሆናል፡፡

በዚህ የቤት እድሳት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ፤ የለሚ ኩራ ክፍለ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ ቶላ ፤ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ባዩማ ወርቁ እና በየደረጃው ያሉ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

በመርሀ ግብሩ የቤት እድሳት የተደረገላቸው አርሶ አደር ወ/ሮ ብርቱኳን መስቀሌ እድሜአቸው 65 ሲሆን የስምንት ልጆች እናት ናቸው፡፡ እንዲህ እንደ ዛሬው አቅማቸዉ ሳይደክም ከራስ አልፎ ለሌሎችም የሚዘረጋ እጅ ዛሬ አቅም አንሶት ጉልበት ደክሞ ከልጆቻቸው እጅ ላይ ከዋሉ አመታት አስቆጥረዋል፡፡ አስተዳደሩ ይህን በመረዳት የተሻለ ማረፊያ ሊሠራ በክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ ግብር  ተግባር አካል አድርጎታል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላት በመርሀ ግብሩ ላይ  ስራዉ እስኪጠናቀቅ በሂደቱ ውስጥ ለሚሳተፉ አካላት በተለይም ደግሞ ለሁለቱ ትምህርት ተቋማ  ላከናወኑት እና ለሚያካነውናቸዉ መልካም ተግባራት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን አያይዘውም በቀጣይ መሠል የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ስራ በትምህርት ተቋማት ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ቢሮ ሀላፊዉ አክለዉም ቤቱ ተሠርቶ ሲጠናቀቅ ሙሉ የቤት እቃው በትምህርት ቢሮ እንደሚሸፈን ቃል ገብተዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

 ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s