የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ክልላዊ ፈተና ላይ በድጋፍና ክትትል ተግባር ለሚሳተፉ የቢሮው ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ሰጠ፡፡
በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ፈተናው ሰላማዊ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ እና በፈተና ሂደቱ የሚያጋጥሙ ችግሮች ቢኖሩ ከቢሮ የተመደቡ ባለሙያዎች መፍትሄ በመስጠት ፈተናው ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ በበኩላቸው በ2014 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ በ179 የመፈተኛ ጣቢያዎች 71,832 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ጠቁመው በየፈተና ጣቢያዎቹ ለድጋፍና ክትትል የተመደቡ ባለሙያዎች የመልስ መስጫ ወረቀቱ በአግባቡ ተሰብስቦ መታሸጉን መከታተል እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል፡፡
ዘንድሮ ፈተናው ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 29/2014 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ ሲሆን በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች 1,800 ፈታኝ ፤450 ሱፐር ቫይዘር፤179 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎችን ጨምሮ በድምሩ 2,429 የፈተና አስፈጻሚዎች መመደባቸውን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!







