የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት የአፍሪካ ህጻናት ቀንን በኒው ኤራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አከበረ፡፡
በመርሀ ግብሩ ተማሪዎችና መምህራንን ጨምሮ ሌሎች የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ አካላት ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ቀኑ ዘንድሮ በህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በጋራ እንከላከል በሚል መሪ ቃል በአህጉራችን ለ32ኛ እንዲሁም በሀገራችን ለ31ኛ ጊዜ ታስቦ መዋሉን በመርሀግብሩ ተገልጻል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ አበባ ዘውዴ እለቱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የአፍሪካ ህጻናት ቀን በ1976 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ በወቅቱ በነበረው የአፓርታይድ ስርአት ሰልፍ በወጡ ተማሪዎች ላይ የፈጸመውን አስከፊ ጭፍጨፋ ለማሰብ እ.አ.አ በ1991 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ባደረገው ስብሰባ በወሰነው መሰረት ቀኑ በመከበር ላይ እንደሚገኝ ገልጸው የጥቃቱ ሰለባዎች በዋናነት ህጻናት ተማሪዎች እንደመሆናቸው ቀኑ በትምህርት ቤቶች መታሰቡ ተማሪዎችን ከመሰል ጥቃት ለመከላከል እንደሚረዳ አስገንዝበዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች እለቱን የተመለከቱ ግጥሞችና ድራማዎችን ጨምሮ የተለያዩ አስተማሪ ፕሮግራሞችን አቅርበዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!







