ቀን 22/10/2014 ዓ.ም

አራብሳ አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ አገልግሎት ተግባራዊ በማድረግ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ትምህርት ቤቱ ተግባራዊ ካደረጋቸው አገልግሎቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር 9715 አጭር የጽሁፍ መልዕክት ማስተላለፊያ መስመርን በመጠቀም ከተማሪ ወላጆች፤መምህራንና ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር በቀላሉ ግንኙነት መፍጠር የተቻለበት አሰራር መሆኑን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ጌትነት ገብረሚካኤል ገልጸው አገልግሎቱም በትምህርት ቤት ደረጃ ተግባራዊ ሲደረግ በአዲስ አበባም ሆነ በሀገር በአቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡ 

ርዕሰ መምህሩ አክለውም ትምህርት ቤቱ 8,500 ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ የሚገኝ እንደመሆኑ ቀደም ሲል ከተማሪ ወላጆች ጋር የነበረው ግንኙነት በደብዳቤ ስለነበር ለወረቀትና ቀለም ሲወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ ማስቀርት  ከማስቻሉ ባሻገር የሰው ጉልበትና የማባዣ ማሽን አቅምን በአግባቡ ለመጠቀም መቻሉን ገልጸው ለአገልግሎቱም በወር 2,800 ብር ለኢትዮ ቴሌኮም እንደሚከፈል አስረድተዋል፡፡

ትምህርት ቤቱ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢንተርኔት አገልግሎት በመጀመሩ መምህራን በአይ ሲቲ ላብራቶሪ የሚፈልጉትን መረጃ ማግኘት ከመቻላቸው ባሻገር ትምህርት ቤቱ በውጭ ሀገር ከሚገኙ መሰል ትምህርት ቤቶች ጋር የስራ ግንኙነት ፈጥሮ ልምድ መቅሰም መቻሉን አቶ ጌትነት አስታውቀዋል፡፡

መምህር ዳንኤል መኮንን በትምህርት ቤቱ የሒሳብ ትምህርት መምህር ሲሆኑ ትምህርት ቤቱ አጭር የጽሁፍ ማስተላለፊያ መስመሩን መጠቀም መጀመሩ ከመምህራንም ሆነ ከሌሎች የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ባሉበት በቀላሉ መገናኘት እንዳስቻለው ሲገልጹ ተማሪ ዮርዳኖስ ገብረኪዳን በበኩላ  ቀደም ሲል ከትምህርት ቤት ለወላጆቻቸው የሚላኩ መልዕክቶች በወረቀት እንደነበሩ ገልጻ አሁን ግን በአጭር የጽሁፍ መላኪያ ቁጥሩ በቀላሉ መገናቸት መቻሉን ጠቁማለች ፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

 ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s