ቀን 22/10/2014 ዓ.ም

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች ዉስጥ እንደሚሰጥ ተገለፀ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ  በሆሳዕና ፣ በወራቤና በወልቂጤ ከተሞች የሚገኙ  ሁለተኛ ደረጃና ሞዴል ትምህርት  ቤቶችን  ጎብኝተዋል።

በጉብኚታቸዉ ወቅት ከተማሪዎችና ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር ባደረጉት ቆይታ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በትምህርት ቤቶች ሳይሆን በዩኒቨርስቲ ውስጥ  እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

እንደሚኒስትሩ ገለጻ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በኤሌክትሮኒክስ /online/ መስጠት እስከሚጀመር ድረስ  በዩኒቨርስቲዎች መሰጠቱ ይቀጥላል ።

የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲ እንዲሰጥ የተወሰነው የፈተና ሰርቆትና ማጭበርበርን ለማስቀረት ታስቦ  በመሆኑ ተማሪዎች ትምህርት በስራና በታታሪነት የሚገኝ መሆኑን አውቀው በርትተው መማር ፣ማጥናትና ማወቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርትን ጥራትን ለማሻሻል በአጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፎች ሌሎችንም የተለያዩ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ መሆኑንም ፕሮፌሰር ብርሀኑ መጠቆማቸዉን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል ።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

 ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a comment