የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከተማ አቀፍ የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።
የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕዩ በከተማ ደረጃ ዘንድሮ ለ7ኛ ጊዜ ከሰኔ 9 እስከ 11/2014 ዓ.ም ድረስ “የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የብልጽግና ጉዛችንን በሳይንስና ፈጠራ ዕውን እናደርጋለን!” በሚል መሪ ቃል በወዳጅነት አደባባይ ይካሄዳል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አበበ ቸርነት ከተማ አቀፍ የሳይንስና ፈጠራ ስራ አውደ ርዕዩን አስመልክተው በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕዩ በዋናነት በሳይንስ ፈጠራ የዳበረ ትውልድ መፍጠርን መሰረት አድርጎ እንደሚካሄድና መርሀ-ግብሩም በተማሪዎች መካከል ጤናማ ውድድርን በመፍጠር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡
ዳሬክተሩ አክለውም በአውደ ርዕዩ ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች እንደየ ክፍል ደረጃቸው በተለያዩ ዘርፎች የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ጠቁመው በመርሀ ግብሩ የተሻለ የፈጠራ ስራ ለሚያቀርቡ ተማሪዎችና መምህራን እውቅና እንደሚሰጥ አስረድተዋል፡፡
በአውደ ርዕዩ በሳይንስና ሒሳብ ትምህርቶች ፤ በአይ ሲቲ፤ በልዩ ፍላጎት እንዲሁም በስነ ጥበብ ዘርፎች በተማሪዎችና በመምህራን የሚቀርቡ የፈጠራ ስራዎች የሚቀርቡ ሲሆን በአውደ ርዕዩ የሚቀርቡ የፈጠራ ስራዎችም በየትምህርት አይነቱ በውጤታማነታቸው በተመረጡ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች አወዳዳሪነት ተዳኝተው የተሻሉት በተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እውቅና እንደሚሰጣቸው አቶ አበበ አስታውቀዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!


