የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት በቅርቡ በሚካሄደው የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ላይ በዳኝነት ለሚሳተፉ መምህራን ኦረንቴሽን ሰጠ።
የፈጠራ ስራ ውድድሩ በሳይንስና ሒሳብ ፤ በአይ ሲቲ፤ በልዩ ፍላጎትና በስነ-ጥበብ ዘርፎች በተማሪዎችና በመምህራን የሚቀርቡ የፈጠራ ስራዎችን መሰረት አድርጎ የሚካሄድ ሲሆን በዚህ ውድድር በዳኝነት የሚሳተፉት መምህራን በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች በየትምህርት አይነቱ በውጤታማነታቸው የተመረጡ ናቸው፡፡
በመርሀ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ እንዳስታወቁት በሳይንስና ሒሳብ የፈጠራ ስራ አውደ ርዕዩ የሚቀርቡ የፈጠራ ስራዎች በክፍለ ከተሞች በየትምህርት አይነቱ ተመርጠው የሚቀርቡ መሆናቸውን ጠቁመው ዳኞችም በተዘጋጀው የማወዳደሪያ መስፈርት መሰረት በከፍተኛ ጥንቃቄ የዳኝነት ተግባራቸውን ማከናወን እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
አቶ ጌታቸው አክለውም በተማሪዎችም ሆነ በመምህራን የሚቀርቡት የፈጠራ ስራዎች ከስርዓተ ትምህርቱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው መሆናቸው እንዲሁም ወቅታዊና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ የፈጠራ ስራዎች ስለመቅረባቸው በመስፈርቱ ለዳኝነት ከተቀመጡ ነጥቦች መካከል እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕዩ በከተማ ደረጃ ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ ከሰኔ 9 እስከ 11/2014ዓ.ም ድረስ “የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የብልጽግና ጉዛችንን በሳይንስና ፈጠራ ዕውን እናደርጋለን!” በሚል መሪ ቃል በወዳጅነት ፓርክ ይካሄዳል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!



