ቀን 2/10/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት በስርዓተ ጾታ ክበብ እንቅስቃሴ የተሻለ አፈጻጸም ባላቸው ትምህርት ቤቶች የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም አካሄደ።

የልምድ ልውውጥ ፕሮግራሙ ጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው አጼ ናኩተ ለአብ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና አራዳ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ቤተልሔም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተካሄደ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ከተመረጡ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የስርአተ ጾታ ክበብ አስተባባሪ መምህራንና የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የዘርፈ ብዙ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ አበባ ዘውዴ እንዳስታወቁት የልምድ ልውውጥ መርሀ ግብሩ ተሳታፊዎች በትምህርት ቤቶቹ ከስርአተ ጾታ ክበብ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ ያለውን አፈጻጸም በማየት በየትምህርት ቤቶቻቸው ተግባራዊ ማድረግ እንዲችሉ ታስቦ መዘጋጀግቱን ገልጸው በልምድ ልውውጥ ፕሮግራሙ ተሳታፊ የሆኑ የክበብ ተጠሪ መምህራንም በትምህርት ቤቶቹ ያዩትን የተሻለ እንቅስቃሴ መሰረት በማድረግ ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

የአጼ ናኩተለአብ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የስርአተ ጾታ ክበብ አስተባባሪ መምህርት አይናለም ጥላሁን እና የቤተልሔም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የስርአተ ጾታ አስተባባሪ መምህርት ሰላም ተገኝ ለተሳታፊዎቹ በየትምህርት ቤቶቻቸው ያለውን እንቅስቃሴ የተመለከተ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በዋናነትም ሴት ተማሪዎችን ከጾታዊ ጥቃቶች ለመከላከል የተክናወኑ ተግባራትን ምን እንደሚመስሉና ተማሪዎቹ የወር አበባ በሚያዩበት ወቅት ሞዴስ ከማቅረብ ባሻገር ለማረፊያነት የሚጠቀሙዋቸው ክፍሎች መዘጋጀታቸውን በገለጻቸው አስረድተዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

 ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s