በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ልምድ ልውውጥ ተካሄደ።
የልምድ ልውውጥ ፕሮግራሙ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስተባባሪነት የተካሄደ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ከተለያዩ ሴክተሮች የተውጣጡ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ አበባ ዘውዴ በመርሀ-ግብሩ መክፈቻ እንዳስታወቁት በበጀት አመቱ በስራ ክፍሉ ትምህርት ቤቶች ለጾታዊ ጥቃት ተጋላጭ እንዳይሆኑ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመው ስራ ክፍሉ ውጤታማ እንዲሆን ካስቻሉት ምክንያቶች መካከል የቢሮው አመራሮች ለዘርፉ የሚሰጡት ትኩረት ከፍተ ኛ መሆኑና በሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሚደረገው የድጋፍና ክትትል ተግባር የሚጠቀስ መሆኑን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የስርአተ ጾታ ክትትልና ድጋፍ ቡድን መሪ ወይዘሮ ሙሉ አለሙ በበኩላቸው ትምህርት ቢሮ የተሻለ አፈጻጸም ካላቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች መካከል አንዱ መሆኑን መነሻ በማድረግ የልምድ ልውውጥ መርሀ ግብሩ መካሄዱን ገልጸው በዚህ ልምድ ልውውጥ ተሳታፊ የሆኑ የየሴክተር መስሪያ ቤቱ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎችም በትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ ያለውን ውስን በጀት ተጠቅሞ ውጤታማ የሆነበትን መንገድ ልምድ በመቅሰም ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
በስራ ክፍሉ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ሪፖርት በቢሮው የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ባለሙያው በአቶ ደረጀ ደምሴ የቀረበ ሲሆን የልምድ ልውውጡ ተሳታፊዎችም በዳይሬክቶሬቱ ተገኝተው አደረጃጀቱን እና የስራ እንቅስቃሴውን ምልከታ አካሂደዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!





