የሚኪሊላንድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በንባብ ችሎታ ማሻሻል ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።
የሚኪሊላንድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለሶስት ወራት ውስጥ እኔ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማንበብ እችላለሁ! በሚል መሪ ቃል ያሰለጠናቸዉን ተማሪዎች ያስመረቀ ሲሆን መሰል ተግባራት የተማሪዎችን የማንበብ ክህሎት ለማዳበር የሚጫወቱት ሚና የጎላ መሆኑ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተመላክቷል፡፡
በትምህርት ተቋሙ የሚያስተምሩ መምህራን የማንበብ ችግር ያለባቸዉን ተማሪዎች በመለየት እና በሶስት ወር ውስጥ ተማሪዎችን ካለማንበብ ወደ ማንበብ እንዲመጡ የተሰጠ ስልጠና መሆኑ እንዲሁም እኛ መምህራን እያለን በዚህ ትምህርት ቤት አንድም የማያነብ ተማሪ መኖር የለበትም በሚል አስተሳሰብ የተማሪዎችን የንባብ ከህሎት ለማሳደግ መቻሉ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጻል፡፡
በመርሃ ግብሩ የክፍለ ከተማዉ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ት ሳምራዊት ቅባቱ በክብር እንግድነት በመገኘት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በተጨማሪም በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የአሀዱ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን እንዲሁም የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ጥበቡ በለጠ ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ደረጀ ገብሬ እንዲሁም በርከት ያሉ ታዋቂ ግለሰቦች ፣ ምሁራን እና የተመራቂ ተማሪ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!







