ቀን 26/9/2014 ዓ.ም

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት በመምህራን በተካሄዱ የጥናትና ምርምር ስራዎች ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሄደ።

በውይይቱ በክፍለ ከተማው ከሚገኙ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የዲፓርትመንት ተጠሪ መምህራንና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው የትምህርት ባለሙያዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በ7 ርዕሶች የተደረጉ የጥናትና ምርምር ስራዎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

የክፍለከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ተወካይ አቶ ይልማወርቅ ጌታቸው የውይይት መድረኩን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት በክፍለ ከተማው በ2014 ዓ.ም በ30 አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 42 የሚደርሱ የጥናትና ምርምር ስራዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ተካሂደው 7ቱ በዛሬው መድረክ ለውይይት መቅረባቸውን ገልጸው ክፍለ ከተማው የጥናቶቹን ግኝቶች መሰረት በማድረግ ለተግባራዊነታቸውም በትኩረት ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስገንዝበዋል።

አቶ ይልማወርቅ አክለውም የጥናትና ምርምር ስራዎቹ ወቅታዊ በሆኑና ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችሉ ርዕሰ ጉዳዮችን መሰረት አድርገው መካሄዳቸውን ጠቁመው ከ7ቱ ጥናቶች መካከል 2ቱ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአፋን ኦሮሞ ትምህርት ላይ የተደረጉ መሆናቸዉን በማንሳት ክፍለ ከተማውም በዚህ የጥናትና ምርምር ስራ ተሳታፊ ለሆኑ መምህራን ተገቢውን ዕውቅናም ሆነ ሽልማት እንደሚያበረክትና ዛሬ ከቀረቡ የጥናትና ምርምር ስራ መካከል አንዱ ተመርጦ ለትምህርት ቢሮ እንደሚላክም አስታውቀዋል።

መምህር ጉድብ ንጉሴ ካሳ በጥናትና ምርምር ስራው ተሳታፊ ከሆኑ መምህራን አንዱ ሲሆኑ በሰዲል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአማርኛ ቋንቋ የተማሪዎችን የመማር እርካታ ማሻሻል የሚል ርዕሰ ጉዳይን መሰረት አድርገው ጥናት ማካሄዳቸን ገልጸው በጥናቱም በጉዳዩ የተለዩ ክፍተቶችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውን አስረድተዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s