ቀን 22/9/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

ስልጠናው በንብረት አያያዝ ፤ አመዘጋገብና አወጋገድ፤ በፋይናንስ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት እንዲሁም በግዢ ስርአት አፈጻጸም ዙሪያ ከፋይናንስ ቢሮ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት በመጡ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች፤የግዢ እና የፋይናንስ  ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች እንዲሁም ከህንጻ አስተዳደር እና የቢሮው የጨረታ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ የቢሮው ጸሀፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ስልጠናው መመሪያዎችን እና ደንቦችን መሰረት በማድረግ በመስሪያ ቤቱ ያሉ ውስን ሀብቶችና ግብአቶችን  በአግባቡ ለመጠቀም የሚረዳ ግንዛቤ መፍጠር እንዲቻል ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸው የስልጠናው ተሳታፊ ባለሙያዎችም ከስልጠናው የሚያገኙትን እውቀት መሰረት በማድረግ ከንብረት አያያዝም ሆነ ከፋይናንስ አጠቃቀም ጋር በተገናኘ ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የቢሮው የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘነበ አለሙ በበኩላቸው ስልጠናው በዋናነት በንብረት አያያዝ አመዘጋገብና አወጋገድ፤በፋይናንስ አስተዳደር ግልጸኝነትና ተጠያቂነት እንዲሁም በግዚ ስርአት አፈጻጸም ዙሪያ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ተገቢውን ግንዛቤ አግኝተው ተግባራዊ ማድረግ እንዲችሉ በማሰብ መዘጋጀቱን ጠቅሰው ተግባራዊነቱን በተመለከተም  በየስራ ክፍሉ አሰፈላጊው ድጋፍና ክትትል እንደሚካሄድ አስታውቀዋል ፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s