ሳምንታዊ የትምህርት ቤት የፅዳት ንቅናቄ በአደይ አበባ ትምህርት ቤት
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አደይ አበባ ትምህርት ቤት ሳምንታዊ የትምህርት ቤት የፅዳት ንቅናቄ ተካሄደ፡፡
ፅዳት ባህል እንዲሆን በአሁኑ ትዉልድ ላይ የትምህርት ቤት መምህራንና የትምህርት ባለድርሻ አካላት የድርሻቸዉን እንዲወጡና ሰፊውን ስራ እንዲሰሩ መሰል ዘመቻዎች አስፈላጊ መሆናቸዉ እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን የፅዳት ሞዴል ለማድረግ ተማሪዎች ቆሻሻን በየቦታው የሚጥሉ ሳይሆን ቆሻሻን የሚያነሱ መሆን አለባቸውም ተብላል፡፡
በንቅናቀዉ በየቀኑ ከተቋማትና ከህብረተሰቡ ለሚመረተዉ ቆሻሻ የፅዳት ስራውን ህብረተሰብን ማዕከል ተደርጎ ሊሰራ እንደሚገባ የተባለ ሲሆን ፅዳት የስልጣኔ መገለጫ ስለሆነ የመኖሪያ አካባቢንና የትምህርት ቤት አካባቢን ፅዱና ዉብ በማድረግ ተማሪዎች በብሩህ አዕምሮና በጤናማ ህይወት ትምህርታቸዉን እንዲማሩ ማድረግ እጅግ ጠቃሚ መሆኑ ተገልጻል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!





