ቀን 19/9/2014 ዓ.ም

በልደታ ክፍለ ከተማ የሳይንስና ፈጠራ ስራዎች ዐውደ ርዕይ ተካሄደ፡፡

በልደታ ክፍለ ከተማ ”የፈጠራ ስራዎች ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የሳይንስና ፈጠራ ስራዎች ዐውደ ርዕይ ተካሄደ።

በዓውደ ርዕዩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ  አቶ ዳኘው ገብሩ እንደተናገሩት በትምህርት ላይ የሚቀርቡ ዐውደ ርዕይ ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የወሰዱትን ትምህርት ወደ ተግባር የሚቀይሩበትና ተማሪዎች የነገ ማንነታየውን የሚቀርጹበት መሆኑን ጠቁመው በተማሪዎች የቀረቡ የፈጠራ ስራዎች ተጠናክረው በህብረተሰቡ ህይወት ተግባራዊ እንዲሆኑ በማድረግ ርብርብ ልናደርግ ይገባል ብለዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሰፋ ለምቦሶ እንደገለጹት በትምህርት ላይ ለውጥ ስናመጣ በሀገርን ዕድገት ላይ በጎ ተፅዕኖ እናደርጋለን ብለው የትምህርት ዘርፉን በማዘመንና የፈጠራ ስራዎችን በማበረታታት ለችግሮች መፍትሄ የሚፈልጉ ተማሪዎችን እናፈራለን ብለዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት እጅጋየሁ አድማሱ በበኩላቸዉ የህብረተሰቡን ተጠቃማነት በትምህርቱ ዘርፍ ለማረጋገጥ ትምህርት ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑን ገልጸው ዐውደ ርዕዩ የተዘጋጀበት ዓላማም የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ለህብረተሰቡ ችግር ፈች የሆኑ ፈጠራዎችን ለማበረታታት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s