በቦረና ዞን የ8ኛ ክፍል ተማሪው የመንደሩን ነዋሪዎች የመብራት ኃይል ተጠቃሚ አደረገ፡፡
የቦረና ዞን ዋጫሌ ወረዳ ዌቢቲ ቀበሌ ነዋሪው ተማሪ አደን ሁሴን የቱሉ ወቢ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡
ተማሪው የከብቶችን አዛባና የተለያዩ እንሰሳትን እዳሪ በመቀላቀል ባዮጋዛ በማዘጋጀት እንዲሁም ሽቦ እና ፕላስቲክን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ችሏል፡፡
በዚህም ከራሱ የኃይል ፍጆታ አልፎ ለ16 የቀበሌው አባወራዎች መስመር በመዘርጋት የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡
በአካባቢው የሚከናወነውን የባዮ ጋዝ አሠራር መነሻ በማድረግ እና የራሱን የፈጠራ ችሎታ በማከል ውጤታማ ሥራ መሥራቱን ተማሪ አደን ለኦቢኤን ገልጿል፡፡
ተማሪው ካከናወነው የፈጠራ ሥራ በወር 1 ሺህ 600 ብር ገቢ እያገኘ መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡
የተማሪ አደን እናት ወይዘሮ መሱ ሁሴን አደን ስድስተኛ ልጃቸው መሆኑን ገልጸው፥ ነገሮችን የመመራመር እና አዲስ ነገሮች የመፍጠር ዝንባሌ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
የዞኑ የውሀ እና ኢነርጂ ጽሕፈት ቤት በበኩሉ ለተማሪ አደን የፈጠራ ሥራዎች የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ጨምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ማረጋገጡን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግባል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

