ቀን 17/9/2014 ዓ.ም

በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሠለጠኑ 21 ተማሪዎች ተመረቁ።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የሚገኘው የህዳሴ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን እና ቴክኖሎጂ ያሰለጠናቸውን 21 ተማሪዎችን አስመረቀ።

በትምህርት ቤቱ አይሲቲ ክበብ አማካኝነት ላለፉት ስድስት ወራት  ከመደበኛ  ትምህርት ጎን ለጎን  ሲሰጥ የነበረውን መሠረታዊ የኮምፒውተር ትምህርት በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር አጠናቀው ተመርቀዋል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ብርቱካን ግረፍ የተማሪዎች ስልጠና እንዲሳካ ትልቅ አስተዋጾኦ ላደረጉ የክበብ መምህራን እና ድጋፍ እና ክትትል ላደረጉ የትምህርት ቤቱ አመራሮች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የህዳሴ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ሙሉ ሞሴ ትምህርት ቤቱ ከመማር ማስተማሩ ስራ ጎን ለጎን ተማሪዎች በፍላጎታቸው  በክበብ ውስጥ ጠንካራ ተሳትፎ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ የገለጹ ሲሆን በቀጣይ ይህ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ምክትል ርዕሰ መምህር አቶ ገደፋው አንማው የህዳሴ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እየተሠራ መሆንን በመጥቀስ የዚህ አንዱ እና ትልቁ ማሳያ ስራ የዛሬ ተመራቂ ተማሪዎች ብለዋል።

በምረቃው ስነስርዓት ላይ ላቅ ያለ ውጤት ላመጡ የክበብ አባላት እና መምህራን የምስክር ወረቀት የተሠጣቸው ሲሆን የወረዳ 2 ትምህርት ኃላፊ ፣ የትምህርት ቤቱ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችና አመራሮች ፣ መምህራን ፣ ተማሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s