ቀን 13/9/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻልና አጠቃላይ ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት በተሻሻለው የትምህርት ቤት መሻሻል መርሀ ግብር ማዕቀፍ ዙሪያ በተግባር የተደገፈ ስልጠና መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ስልጠናውን ከኢፌድሪ ትምህርት ሚኒሰቴር የመጡ የትምህርት ቤት መሻሻል ባለሙያዎች በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን በስልጠናው የክፍለ ከተማ የትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎችን ጨምሮ የክላስተር ሱፐርቫይዘሮችና የወረዳ የትምህርት ቤት መሻሻል ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻልና አጠቃላይ ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት ተወካይ  አቶ አብይ ተፈራ በስልጠናው መክፈቻ እንዳስታወቁት የትምህርት ቤት መሻሻል ስትራቴጂክ እቅዱ ተሻሽሎ መዘጋጀቱን ተከትሎ ሰልጣኞች ተገቢውን ግንዛቤ በመያዝ የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እቅድ ማዘጋጀት እንዲችሉ ታስቦ  ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልጸው ስልጠናው በተግባር የተደገፈ ብሎም ከትምህርት ሚኒስቴር በመጡ ባለሙያዎች የሚሰጥ እንደመሆኑ ሰልጣኞች በየክፍለ ከተሞቻቸው ለሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ተመሳሳይ ግንዛቤ መፍጠር እንዲችሉ የሚያግዛቸው መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የቢሮው የትምህርት ቤት መሻሻል ባለሙያው አቶ ሳሙኤል አየለ በበኩላቸው ስልጠናው በተሻሻለው የትምህርት ቤት መሻሻል መርሀ ግብር እቅድ እና በአጠቃላይ የኢንስፔክሽን ማዕቀፍ ዙሪያ አስፈላጊውን ገንዛቤ በመፍጠር በትምህርት ቤቶች የአንድ ዓመትና የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ለማዘጋጀት እንዲረዳ ታስቦ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s