የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት በክፍለ ከተማው በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የተዘጋጀ የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ በቦሌ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ አካሄደ።
በአውደ ርዕዩ ተማሪዎች በሳይንስና ሒሳብ ትምህርቶች ጨምሮ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በስዕል፣ ቅርጻ ቅርጽና በተለያዩ የስነ ጽሁፍ ስራዎች የሰሩዋቸው የፈጠራ ውጤቶች ቀርበው በተለያዩ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተጎብኝተዋል።
በመርሀ ግብሩ መክፈቻ የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ታጋይቱ እባቡ ባስተላለፉት መልዕክት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት ወደ ተግባር ቀይረው በዚህ መልኩ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለዕይታ ማቅረባቸው ለሀገራችን እድገትና ሁለንተናዊ ብልጽግና የማይተካ ሚና ያለው ተግባር መሆኑን ጠቁመው የፈጠራ ስራዎች በዚህ መልኩ በተማሪዎችና መምህራን መዘጋጀታቸው አንዱ ከሌላው ልምድ ለመቅሰም እንደሚረዳውም አስገንዝበዋል።
የቦሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ መስፍን ሀይሌ በበኩላቸው ተማሪዎችም ሆኑ መምህራን የሰሩት የፈጠራ ስራ በቀጣይ ለሀገሪቱ ችግር መፍትሄ መስጠት የሚያስችል ተግባር በመሆኑ ከሚመለከተው አካል አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ገልጸው የክፍለ ከተማው አስተዳደርም ለትምህርት ሴክተሩ ተገቢውን እገዛ ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!













