የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ለክፍለ ከተማ የማህበሩ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀን የሚሰጥ ሲሆን በስልጠናው በየዘርፉ በተከናወኑ ተግባራት እንዲሁም በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ የተጠቀሰ ሲሆን በተጨማሪም አመራሮቹ ሙያዊ አቅማቸውን ማጎልበት በሚችሉባቸው የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።
በስልጠናው መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቅአለም ቶሎሳ እንዳስታወቁት ስልጠናው በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚገኙ የማህበሩ ስራ አስፈጻሚዎች አቅማቸውን አጎልብተው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸው በተጨማሪም ስልጠናው የማህበሩ አመራሮች በየዘርፉ የሚያከናውኗቸውን የተለያዩ ተግባራት በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ማከናወን እንዲችሉ የሚያግዛቸውን ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንደሚረዳቸውም አስገንዝበዋል።
ፕሬዘዳንቱ አክለውም ቀደም ብሎ የማህበሩ የከተማ ስራ አስፈጻሚዎች ተመሳሳይ ስልጠና መውሰዳቸውን ጠቁመው የስልጠናው ተሳታፊዎችም በስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት በማድረግ የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ እና ልዩ ልዩ መመሪያዎች በአግባቡ ተግባራዊ መደረጋቸውን ክትትል ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!



