ቀን 8/9/2014 ዓ.ም

መልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ “በተለወጠ ሲቪል ሰርቪስ የከተማችንን አገልግሎት አሰጣጥ እናረጋግጣለን” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ከቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች ጋር ውይይት አድርጓል ::

ውይይቱ በከተማዋ እየተስተዋሉ ያሉ የመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በተመለከተ እያንዳንዱ ሰራተኛ ምን ይጠበቅበታል በሚሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጓል ::

በውይይቱ ላይ ተልእኮን መወጣት የሚያስችል አስተሳሰብ እውቀትና ክህሎት በመገንባት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በመለየትና በመፍታት በግልፀኝነትና ተጠያቂነት ስርአትን በጥብቅ ዲሲፕሊን መምራት እንደሚገባ ተብራርቷል ::

በውይይቱ የተሳተፉ ሰራተኞችም እንደከተማ እና ቢሮው የሚታዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ያሏቸውን ነጥቦች አንስተው ሰፊ ውይይት አድርገዋል ::

የትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛው ገብሩ በቢሮው የተራራቀ የስራ አፈፃፀም መኖሩን ጠቁመው ይህን ለማቀራረብ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣና ሁሉም የስራ ሰዓቱ አክብሮ የአገልግሎት አሰጣጡን እንዲያሻሽል አሳስበዋል ::

የቢሮ ጽፈት ቤት ሀላፊ የሆኑን አቶ ስሳይ እንዳለ የመወያያ ሰነዱን ካቀረቡ በሀላ ሁሉም ሰራተኛ ግልጽ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠጥ ተግቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s