የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በወቅታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከምሁራን ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በወቅታዊ እና ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ‘’ያለዜጎች ቀጥተኛ ተሳትፎ በሁሉም መስክ የተሳካላት አገር መፍጠር አይቻልም!’’ በሚል መሪ ቃል ከምሁራን ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ እንደገለፁት ያለምሁራን ቀጥተኛ ተሳትፎ የሚረጋገጥ የሀገር ብልጽግና ሰለማይኖር መሰል መድረኮችን ማከናወን ያስፈልጋል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘላለም ሙላቱ የመድረኩን የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል። በጥቂት ተዋንያን ብቻ ታላቅ ሀገር መገንባት ያዳግታል ያሉት የቢሮ ሀላፊ የዳር ተመልካች ከመሆን በመውጣት የራስን ሚና በመወጣት እና በመተባበር ለላቀ እድገት መትጋት ይገባል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳኛዉ ገብሩ በበኩላቸዉ በጋራ በሆነዉ ጉዳያችን ላይ ይሉኝታ አያስፈልግም ያሉ ሲሆን ሀገር ተረካቢ የሆኑ ዜጎችን የመፍጠር ስራችን ውጤታማ እንዲሆን በትኩረት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ የቢሮ ማኔጅመንት አባላት እና ዳይሬክተሮች ፣ ርዕሰ መምህር ፣ ሱፐርቫይዘሮች ፣ መምህራን ፣የክፍለ ከተማ ቡድን መሪዎች ፣ የግል ትም/ቤት ባለሀብቶች እና የክፍለ ከተማ ት/ፅ/ቤት ኃላፊዎች ተሳታፊ ሁነዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!