“ትምህርት ቤቴን አፀዳለሁ፤ ፅዱና ውብ በሆነ ከተማ እኖራለሁ!!”
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 በሚገኘው ሐዋሪያው ጴጥሮስ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የጽዳት ዘመቻ ተከናወነ።
የጽዳት ዘመቻውን ያስጀመሩት በአዲስ አበባ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መለሰ ዓለሙ አዲስ አበባን ውብና ጽዱ የማድረግ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ የነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎችም አካባቢያቸውን ውብ እና ጽዱ የማድረግ ተግባርን እንደ ጥሩ ባህል እና ልማድ ይዘው እንዲያድጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ከጽዳት ዘመቻው ጎን ለጎን ከወዳደቁ ደረቅ ቆሻሻ የተሰሩ በተማሪዎች የተዘጋጀ የመልሶ መጠቀም ስራዎችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ ለዕይታ ቀርቧል።
በጽዳት ዘመቻ መርሃ ግብሩ ላይ አቶ መለሰ ዓለሙን ጨምሮ የአዲስ አበባ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ ፣ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ፣ የከተማ፣ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች፣ የፅዳት አምባሳደሮች እንዲሁም አጠቃላይ የት/ቤቱ ማህበረሰብ በተገኙበት ተከናውኗል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!




5,919
People reached
223
Engagements
5555
2 Shares
Like
Comment
Share