ቀን 5/9/2014 ዓ.ም

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ትምህርትቤቶች መካከል ሳይንስና የሂሳብ ትምህርት የፈጠራ ስራ ውድድር ተካሄደ፡፡

በአውደ ርዕዩ በክፍለ ከተማው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በተፈጥሮ ሳይንስ፣በሒሳብ፣በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣በስነ ጽሁፍ እንዲሁም በስእልና ቅርጻቅርጽ የሰሩዋቸው የፈጠራ ስራዎች ለእይታ ቀርበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ተጠሪ የሆኑት አቶ መለስ አለሙ በመርሀ ግብሩ ተገኝተው እውቀት በተግባር ሲደገፍ ከትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ባሻገር ሃገራችን ያለባትን ችግር ለመቅረፍና ከፍተኛ የሆነ የዕድገት ማማ ላይ ለማድረስ ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አክለውም የነገ ሃገር ተረካቢ ዜጎች የሚፈጠሩት ትምህርት ቤት ነው ስለሆነም ሁላችንም በትጋት ኃላፊነታችንን መወጣት አለብን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው የንድፈሃሳብ ትምህርት በተግባር ሲደገፍ የትምህርት ጥራትን ያረጋግጣል፤ ተማሪዎች ሃገር ማልማት ላይ ያላቸውን አስተዋዕጾ ከፍ ያደርጋል፤ በተጨማሪም ተማሪዎች ክህሎታቸውን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋዕጾ አለው ሲሉ ገልጸዋል ፡፡

የውድድሩ ተሳታፊ የሆኑ ተማሪዎችም የፈጠራ ስራ አውደርዕይ መዘጋጀቱ ከመደበኛው ትምህርት ባሻገር የፈጠራ ክህሎታችንን ተጠቅመን ስራ ፈጣሪነትን እንማርበታለን፤በዩኒቨርስቲ ደረጃ ትምህርታችን ስንጨርስ የመንግስት ስራን ከመጠበቅ ይልቅ ክህሎቶቻችንን በመጠቀም በራሳችን ስራ ፈጥረን እንድንሰራና እራሳችንንና ሃገራችንን ለማሳደግ ከፍተኛ የሆነ ሚና አለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

መምህራን በበኩላቸው ይህ አውደርዕይ ተማሪዎች የፈጠራ ስራቸውን እንዲያዳብሩ ከማድረጉ ባሻገር በየአካባቢው የተጣሉ ቆሻሻዎች መልሶ ጥቅም ላይ ማወልንና አካባቢን ለማጽዳት የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።

በአውደ ርዕዩ ቀደም ብሎ በትምህርት ቤትና ወረዳ ደረጃ በተካሄዱ የሳይንስና ፈጠራ ውድድሮች አሸናፊ ሆነው የተመረጡ የመንግስትና የግል የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የውድድሩ ነገ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

+27

6,678

People reached

305

Engagements

Boost post

6262

2 Comments

2 Shares

Like

Comment

Share

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s