ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በየካ አባዶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፡፡
የማለዳ ስፖርት ሥስተኛ ዙር ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በዛሬው እለት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር ስር በሚገኘው በየካ አባዶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከናውኗል።
በመድረኩ የተማሪዎች የማለዳ ስፖርት እንቅስቃሴ ተማሪዎች ከትምህርት ጎን ለጎን ስፖርቱን የሁል ጊዜ ልምድ እንዲያደርጉት እና ወደ ትምህርታቸው ሲመለሱ የነቃ አእምሮ ይዘው ትምህርታቸውን በንቃት እንዲከታተሉ እንደሚረዳም ተገልጿል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ግርማ በንግግራቸው ተማሪው በስፖርት የሠለጠነ ንቁ አዕምሮ እንዲኖረው እና ከአጉል ልምዶች ራሱን በመጠበቅ ለሀገር እና ለወገኑ ጠቃሚ ዜጋ እና ከሀገር ወዳድነት በተጨማሪም ስራ ፈጣሪ እንዲሆን ይረዳል ብለዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!




