ቀን 29 /8/2014 ዓ.ም

8ኛው  ከተማ አቀፍ የትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር ” በአካልና በአእምሮ የዳበረ ትውልድ ለአገር ግንባታ ” በሚል መሪ ሀሳብ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 07 ሮም ሜዳ በድምቀት  ተጀመረ ።

በአዲስ አበበ ከተማ ለ8ኛ ጊዜ ” በአካልና በአእምሮ የዳበረ ትዉልድ ለአገር ግንባታ ”  በሚል መሪ ቃል ከሚያዚያ 29 እስከ ግንቦት 14/2014 ዓ.ም በሚካሄደዉ ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፖርታዊ ዉድድር ከ 2ሺህ በላይ ተማሪዎች በ7 የስፖርት ዐይነቶች ይወዳደራሉ ።

የአደስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ የሚያዘጋጁት ይህ 8ኛዉ ከተማ አቀፍ  የተማሪዎች ስፖርታዊ ዉድድር ዛሬ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7  በሚገኘዉ ሮም_ሜዳ /ሁለገብ የስፖርት ማዘዉተሪያ ስፍራ/ ተጀምሯል ።

በፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ  ትምህርት ለአንድ ሀገር ቁልፍ የልማትና የዕድገት መሠረት በመሆኑ ፣ ስፖርትም በአካል ፣ በአእምሮና በስነ ልቦና የታነፀ ትውልድ መፍጠሪያ በመሆኑ  ዋና ግብ በማድረግ  ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል ።

የተማሪዎች ስፖርታዊ ውድድር የነገ የሀገር ተተኪና  ታዳጊ ወጣቶችን ማፍለቂያ በመሆኑ ተማሪዎች በቆይታቸው በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነትና ስነ ምግባር እንዲወዳደሩ በአዳራ ጭምር ያሳሰቡት አቶ ዘላለም ለፕሮግራሙ መሳካት ከትምህርት ቢሮ ጋር በመቀናጀት ለሚያዘጋጀው  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ  እና  ለአስተናጋጁ ለኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል ረዲ በበኩላቸው የ8ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፖርታዊ ውድድር ክፍለ ከተማዉ በአስተናጋጅነት እንዲመረጥ ዕድሉን ለሰጡ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት እና ትምህርት ቢሮዎች በነዋሪውና በራሳቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በበኩላቸው በ8ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፖርታዊ ውድድር ላይ ከ11ዱ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ከ2ሺህ በላይ ተማሪዎች በ7 የስፖርት ዐይነቶች ውድድራቸውን እንደሚያካሂዱ ገልፀዋል ።

በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ በተለያዩ የኪሎ ካታጎሪ የቦክስ ውድድር ተጀምራል ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ በዉድድሩ የሚሳተፉት የ11ዱም ክፍለ ከተማ  ስፖርተኞች፣  የከተማዉና የክፍለ ከተማ ከፍተኛ የስራ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸዉ ስፖርተኞችና የስፖርት ቤተሰቦች ታድመዋል ።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s