የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ለስርዓተ ጾታ ክበብ ተጠሪ መምህራን እና ለክፍለ ከተማ ዘርፈ ብዙ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።
የቢሮው የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሯ ወይዘሮ አበባ ዘውዴ በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ቤቶች አከባቢ ተማሪዎችን ለተለያዩ ጾታዊ ጥቃቶች የሚያጋልጡ ጉዳዮች አለመቀረፋቸውን ገልጸው እነዚህን አንገብጋቢ ችግሮች ለመቅረፍ በየትምህርት ቤቱ የተቋቋሙ የስርዓተ ጾታ ክበባት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ስልጠናው ለክበብ ተጠሪ መምህራኑ ግንዛቤ መፍጠርን ታሳቢ አድርጎ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
በዳይሬክቶሬቱ የስርዓተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ባለሙያው አቶ ደረጀ ደምሴ በበኩላቸው በየትምህርት ቤቱ የሚገኙ የስርአተ ጾታ ክበብ ተጠሪ መምህራን በትምህርት ቤት አከባቢ የሚስተዋሉ ጾታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል የሚያስችላቸውን እቅድ ማዘጋጀት እንዲችሉና ያከናወኑዋቸውን ተግባራት ለሚመለከተው አካል በአግባቡ ሪፖርት ለማድረግ የሚያግዛቸውን ግንዛቤ ከስልጠናው እንደሚያገኙ ገልጸዋል።
ስልጠናውን ከትምህርት ሚኒስተር በመጡትና በዘርፉ የካበተ የማሰልጠን ልምድ ባላቸው አቶ እስክንድር ላቀው የተሰጠ ሲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎችም የቀረቡ የስልጠና ርዕሰ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ ሰፊ ተሳትፎ አድርገዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!






