ቀን 28 /8/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻልና ሱፐር ቪዝን ዳይሬክቶሬት የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ስራ ክፍል በተቋማት ቫይረሱን ለመከላከል በወጣ ደንብ ዙሪያ ውይይት አካሄደ ፡፡

በውይይቱ ለኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ የሚረዳ ገንዘብ ከደሞዛቸው በመቁረጥ ላይ የሚገኙ የቢሮው ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በውይይቱ መክፈቻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻልና ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ አብይ ተፈራ እንዳስታወቁት በትምህርት ሴክተሩ ከሚከናወኑ በርካታ ተግባራት መካከል አንዱ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ መሆኑን ገልጸው የቢሮው ሰራተኞችም ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል በሚደረገው እንቅስቃሴ የበኩላቸውን ኃላፊነት ለመወጣት በማሰብ ከደሞዛቸው በመቁረጥ ለሚያደርጉት አስተዋጽኦ ምስጋና ከማቅረባቸው ባሻገር እስካሁን ድጋፉን ማድረግ ያልጀመሩ ሰራተኞችም በተመሳሳይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል፡፡ 

የቢሮው የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ባለሙያዋ ወይዘሪት ገንዘብ ደሳለኝ በመንግስት መስሪያ ቤቶች የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመከላከል በአዲስ አበባ ምክር ቤት በወጣ መመሪያ ዙሪያ ሰፋ ያለ ገለጻ ደረጉ ሲሆን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች  ደሞዝ በሚቆረጥ ገንዘብ አራት ወላጆቻቸውን በዚሁ ቫይረስ ላጡ ህጻናት በቃሚነት ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s