ቀን 13/8/2014 ዓ.ም

በ3ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል የንባብ ክህሎት የጥያቄ እና መልስ ውድድር ተካሄደ፡፡

በኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ እና ፔስታሎዚ የህፃናት መርጃ ድርጅት /PCF/ የትምህርት ፕሮጀክት አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች የንባብ ክህሎት የጥያቄና መልስ ውድድር በኮተቤ ብርሃነ ህይወት ቅ/አ እና የመ/ደረጃ ትምህርት ቤት አሸናፊነት ፍፃሜውን አግኝቷል::

በኮልፌ ቀራኒዮ ፣ በአዲስ ከተማ ፣ በለሚ ኩራ እና በየካ ክፍለ ከተማዎች በሚገኙ 8 ትምህርት ቤቶች ማለትም አባዶ ፣ የካ ጣፎ፣ ኮተቤ ብርሀነ ህይወት፣ ንጋት ኮከብ፣ አቡነ ባስሊዎስ፣ የማነ ብርሃን፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ እና አስኮ አዲስ ሰፈር መካከል በሶስት ዙር ሲካሄድ በቆየው ውድድር ተማሪ ሶስና ስምዖን ከየካ ከፍለ ከተማ ከኮተቤ ብርሃነ ህይወት ቅ/አ/ እና የመ/ደረጃ ትምህርት ቤት አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ተማሪ ያፌት ይመር ከለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ ከየካ አባዶ ትምህርት ቤት እና ተማሪ ተመስገን አለማየሁ ከየካ ከፍለ ከተማ ንጋት ኮከብ ትምህርት ቤት 2ኛ እና 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል።

በዙር ውድድሩ እንዲሁም በፍፃሜው አሸናፊ በመሆን ከ1-3ኛ ለወጡ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ቦርሳ፣ የፅህፈት መሳሪያ ፣ መዝገበ ቃላት እና የንባብ ክህሎታቸውን የሚያግዙ የተለያዩ የማጣቀሻ መፅሃፍት ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን በፍፃሜ ውድድሩ አሸናፊ ለሆነው የኮተቤ ብርሃነ ህይወት ትምህርት ቤት የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶለታል።

በውድድሩ ፍፃሜ የተገኙት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ደመላሽ አድማሱ ለተወዳዳሪ ተማሪዎች እና ለመምህራን ባስተላለፉት መልእክት የውድድሩ ዋነኛ ግብ የተማሪዎችን የንባብ ክህሎት ማዳበር እና አወንታዊ የሆነ የፋክክር መንፈስ በመገንባት የንባብ ፍቅርን እና ተነሳሽነት ማጎልበት መሆኑን በመጥቀስ በውድድሩ የተሳተፉ ተማሪዎች በሙሉ አሸናፊዎች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ 

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s