የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ለመላዉ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረዉን የትንሳኤ በዓልን አስመልክተዉ ባስተላለፉት የእንኳን በሰላም አደረሳችሁ መልዕክታቸዉ በአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሰጠዉ የአጠቃላይ ትምህርት ውጤታማነትን ለማረጋገጥ እንዲቻል በተለይም ደግሞ በ2014 የትምህርት ዘመን በየደረጃዉ በተከናወኑ ተግባራትና በተደረጉ ርብርቦች ተጨባጭ የሆኑ የትምህርት ልማት ስራ ውጤቶች መታየት ላይ መሆናቸዉን ገልጸዉ በዚህ ሂደት የተማሪዎች ፣ የመምህራን ፣ የወላጆች ፣ የትምህርት ባለሙያዎች እና አመራሮች ሚና የጉላ በመሆኑ ለትምህርት ማህበረሰቡ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ከዚህ የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ሁለንተናዊ ስብዕናው የተማላ ሀገር ተረካቢ ትውልድ መፍጠር እንዲቻልም ሁሉም አካል በትጋት ይስራ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሰላማዊ የመማር ማስተማር አካባቢ በመፍጠር ፣ ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን በመቅረጽ እና ለሀገር እድገት አስተዋጽዎ የሚያበረክቱ የሀገር መሰረቶችን በማፍራት ተግባር ውስጥ አሁንም በልዩ ትኩረት ልንሰራ ይገባል ያሉት ሀላፊዉ የትምህርት ባለድርሻ አኳላት የትንሳዩ በዓልን ሲያከብሩ እራሳቸዉን ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመጠበቅ የሚያስችሉ የመከላከያ መንገዶችን በመተግበር ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ቢሮ ሀላፊዉ አክለዉም የትንሳኤ በዓልን ስናከብር አቅመ ደካሞችን እና የታመሙትን የምንጠይቅበት ፣ ዕርስ በዕርሳችን የምንከባበርበትና የምንደጋገፍበት ሊሆንም ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳዩ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የጤና እና የመረዳዳት እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
