ቀን 12/8/2014 ዓ.ም

በ2014 ዓ.ም የተለያየ የክፍያ ጭማሪ ያደረጉ የትምህርት ተቋማት በ2015 ዓ.ም ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ በነበረው ይቀጥላሉ ተባለ፡፡

የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን የግል የትምህርት ተቋማት የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪን  አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሕይወት ጉግስ እንደገለጹት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከአጠቃላይ የግል የትምህርት ተቋማት ጋር በመማር ማስተማር ሂደቱ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመው ከነዚህም ውስጥ በከተማ አስተዳደሩ በአዋጅ 74/2014 በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት ተቋማት የሚያስከፍሉት ክፍያ የወላጅን የመክፈል አቅም ያገናዘበ እንዲሆን የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለዚህም ፍታሐዊ የንግድ ውድድሩን እና የሸማቾች መብት ጥበቃ ማዕከል ባደረገ መልኩ የግል ትምህርት ቤቶች የሚመሩበት የክፍያ ጭማሪ ማንዋል በማዘጋጀት ከግል የትምህርት ተቋማት ማህበር ጋር በመወያየት መግባባት መፈጠሩን አሳውቀዋል፡፡

በተዘጋጀው ማንዋል መሰረት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከወላጅም ከተቋማትም የሚነሱ ጥያቄዎችን ሕግና ስርአት ተከትለው እንዲፈጸሙ የማግባባት ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ በዚህም የማግባባት ስራው የሚሰራው አዋጆችን እና መመሪያን መሰረት በማድረግ ነው ብለዋል፡፡

በ2014 ዓ.ም በነበረው የትምህርት ዘመን 1077 ትምህርት ቤቶች የተለያየ የክፍያ ጭማሪ አድርገዋል ፤ በመሆኑም አሁን ያለው የኢኮኖሚ ግሽበት እና የኑሮ ውድነት ተቋማቱም ላይ ማህበረሰቡም ላይ ጫና በመፍጠሩ 2014 ጭማሪ ያደረጉ ተቋማት ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ 2015 ዓ.ም በነበረው እንዲቀጥል መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በአንፃሩ በ2014 ምንም አይነት ጭማሪ ሳያደረጉ የቆዩ ተቋማት ፕሮፐዛል በመቅረጽ የክፍያ ጭማሪ ምክንያታቸውን ዝርዝር በማቅረብ ከወተመህ ጋር በመወያየት እና ከወላጅ ጋር ዝርዝር ውይይት እንዲያደርጉ ተደርጎ መግባባት ላይ ከደረሱ ውሳኔውን ለባለስልጣኑ በማቅረብ ውሳኔ የሚሰጥበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህም በሚደረጉ ውይይቶች ላይ ወላጆች ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል ፡፡

በትምህርት ቤቶች የመመዝገቢያ ክፍያ የሚከፈለው ከወርሐዊ ክፍያ መሰረት በማድረግ 25% ብቻ መሆን አንደሚገባው አስገንዝበዋል ከዚህ ውጪ የሚያስከፍሉ ተቋማት ካሉ ሕብረተሰቡ መረጃዎችን ለባለስልጣኑ መስጠት እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡

የግል ት/ቤቶች ለትምህርት ተደራሽነት እና ለአጠቃላይ ለትምህርት ጥራቱ ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረጉ ሲሆን በከተማችን በአሁኑ ሰዓት 43% የሚሆኑት ተማሪዎች በግል ት/ቤቶች ውስጥ እንደሚማሩ በጋዜጣው መግለጫ ተመላክቷል ፡፡

ለጥቆማ ነጻ የስልክ መስመር 9302 መጠቀም ይቻላል ተብላል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s