ቀን 7/8/2014 ዓ.ም

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በሚማሩ ተማሪዎች የሳይንስና ፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ተካሄደ።

በአውደ ርዕዩ ቀደም ብሎ በትምህርት ቤትና ወረዳ ደረጃ በተካሄዱ የሳይንስና ፈጠራ ውድድሮች አሸናፊ ሆነው የተመረጡ የመንግስትና የግል የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በመርሀ ግብሩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በተማሪዎች የሚሰሩ የሳይንስና ፈጠራ ስራዎች  የኢትዮጵያን መጻኢ እጣ ፈንታ በመወሰን በኩል የጎላ ሚና እንዳላቸው ጠቁመው ተማሪዎቹ ይህን የመሰለ ስራ ሰርተው ለዕይታ እንዲያበቁ በማድረጉ በኩል ኃላፊነታቸውን በአግባቡ የተወጡ መምህራን ምስጋና እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛው ገብሩ በበኩላቸው በተማሪዎች በዚህ መልኩ ለእይታ የሚቀርብ የሳይንስና ፈጠራ ስራ ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት በተግባር የሚያሳዩበትና በተማሪዎች መካከል ጤናማ ውድድር የሚፈጥር  መርሀ ግብር መሆኑን ገልጸው በክፍለ ከተማ  አሸናፊ የሆኑ ተማሪዎች በቀጣይ በአዲስ አበባ ደረጃ በሚካሄደው ከተማ አቀፍ የፈጠራ ስራ ውድድር ተሳታፊ እንደሚሆኑ አስረድተዋል።

የሳይንስና የፈጠራ አውደ ርዕዩ ቀደም ብሎ በክፍለ ከተማው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተካሂዶ አሸናፊ የሆኑ ተማሪዎች የተሳተፉበት መርሀ ግብር መሆኑን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ባዩማ ወርቁ ጠቅሰው በፕሮግራሙ ተማሪዎቹ በተፈጥሮ ሳይንስ፣በሒሳብ፣በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣በስነ ጽሁፍ እንዲሁም በስእልና ቅርጻቅርጽ የሰሩዋቸው የፈጠራ ስራዎች ለእይታ  መቅረባቸውን ገልጸዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s