“ትምህርት ቤቴን አፀዳለሁ ፅዱ እና ውብ በሆነ ትምህርት ቤት እማራለሁ” በሚል መሪ ቃል 5ኛ ሳምንት የትምህርት ቤቶች የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ፡፡
በኮልፌ ቀራኒያ ፣ በለሚ ኩራ ፣ በአራዳ ፣ በጉለሌ አና በንፋስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማዎች ውስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ “ትምህርት ቤቴን አፀዳለሁ ፅዱ እና ውብ በሆነ ትምህርት ቤት እማራለሁ” በሚል መሪ ቃል 5ኛ ሳምንት የትምህርት ቤቶች የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ፡፡
በኮልፌ ቀራኒዩ ክፍለ ከተማ በአዲስ ህይወት የመጀመሪያ ደረጃ ፣ በለሚ ኩራ በአራብሳ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ፣ በአራዳ በራስ አበበ አረጋይ አፀደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ፣ በጉለሌ በቃሌ የመጀመሪያ ደረጃ እና በንፋስልክ ላፍቶ በጎፋ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ “ትምህርት ቤቴን አፀዳለሁ ፅዱ እና ውብ በሆነ ትምህርት ቤት እማራለሁ” በሚል መሪ ቃል 5ኛ ሳምንት የትምህርት ቤቶች የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ፡፡
በመርሃ ግብሮቹ ትምህርት ቤቶችን የእውቀት መፍለቂያ ብቻ ሳይሆን የጽዳት ተምሳሌት ማድረግና የጽዳት አምባሳደር የሚሆኑ ትውልዶችን ማፍራያ እንዲሆኑ መስራት ተገቢ መሆኑ ተመላክቷል። በተጨማሪም ጤናው የጠበቀ ተማሪ ለማፍራት ትምህርት ቤቶቻችንን ማፅዳትና ፅዳትን ባህል ማድርግ እንደሚገባም ተጠቁሟል ።
በተጨማሪም በትምህርት ቤቶቹ ውስጥ በተማሪዎችና በመምህራን የተዘጋጅ አዝናኝ ድራማዎች እና ግጥሞች ቀርበዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
