የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ፊታውራሪ ላቀአድገህ ክላስተር ማዕከል በ12 ክፍል ተማሪዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር አካሄደ።
በተደረገው የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር ላይ የክፍለ ከተማዉ ት/ጽ ቤት ሀላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ ፣ በክላስተሩ የሚገኙ የ12ኛ ክፍል ተወዳዳሪ ተማሪዎች፣ ተጠባባቂ ተማሪዎች፣ የት/ቤቶች ርዕሳነ መምህራን እና የትምህርት ጽ/ቤት ሱፐርቫይዘሮች ፣ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ እንደገለጹት በሥነ-ምግባር የታነፀና ውጤታማ የሆነ ትውልድ ለማፍራት መሰል ጥያቄና መልስ ውድድሮች አዎንታዊ ተፅእኖ ይኖራቸዋል ሲሉ ገልፀዋል ።
በጥያቄና መልስ ውድድሩ አሸናፊ ለሆኑ ተቋማትና ተማሪዎች የዋንጫና የምስክር ወረቀት ሽልማት የተበረከተ ሲሆን በ1ኛ ደረጃ ስኩል ኦፍ ቱሞሮ ፣ በሁለተኛ ደረጃ ንዋይ ቻሌንጅ ፣ በ3ኛ ደረጃ ሚካኤል ሁለተኛ ደረጀ ት/ቤቶች የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ውድድሩን ያጠናቀቁ ሲሆን አሸናፊ ትምህርት ቤቶች እና ተማሪዎች ከክፍለ ከተማዉ ትምህርት ጽፈት ቤት የተዘጋጀላቸዉን ሽልማት የተረከቡ መሆኑን ከክፍለ ከተማዉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያሰያል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
